በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች(FAQ)፦
ስለ የዲሲ ስትሪትካር (DC Streetcar) አገልግሎት እና ከሌሎቹ በከተማው ውስጥ ከሚሰጡ የመጓጓዣ አገልግሎቶች ጋር ሲነፃጸር ምን እንደሚመስል የበለጠ ይውቁ። የስትሪትካር ሊንጎ ላይ የቅርብ መረጃ ለማግኘት የ የዲሲ ስትሪትካር የቃላት መፍቻን ይመልከቱ።
ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች – ስለ ስትሪትካር አገልግሎት እና ስምሪቶች
በስትሪትካር መጓዝ ምን ያህል ያስከፍላል?
ዲሲ ስትሪትካር አገልግሎቱን የሚሰጠው በነፃ ነው። ዲዶት [DDOT] የትራንስፓርት መጓጓዣ ላይ የታሪፍ ተመን ፖሊሲውን እስካልቀየረ ድረስ ዲሲ ስትሪትካር ለነዋሪዎች እና በመተላለፊያ ቦታው ላይ ለሚመጡ ጎብኚዎች አገልግሎቱን የሚሰጠው በነፃ ነው።
የስትሪትካር አገልግሎት የሚሰጥባችው የስምሪት ሰዓታት የትኛዎቹ ናቸው?
- ከሰኞ-ሐሙስ፦ ከንጋቱ 6:00 am እስከ እኩለ ለሊት 12:00 am ስዓት ድረስ
- አርብ፦ ከንጋቱ 6:00 am እስከ ምሽቱ 2:00 am ሰዓት ድረስ
- ቅዳሜ፦ ከጠዋቱ 8:00 am እስከ ምሽቱ 2:00 am ሰዓት ድረስ
- እሁድ፦ ከጠዋቱ 8:00 am እስከ ምሽቱ 10:00 pm ስዓት ድረስ
ከመሳፈር በፊት የስትሪትካር ተሳፋሪ መጫኛ ቦታ ላይ ምን ያህል ጊዜ መጠበቅ ያስፈልጋል?
የዲሲ ስትሪትካር በግርድፉ 12-ደቂቃ የመጠባበቂያ ጊዜ አለው፣ ይሄም ማለት፣ የተሳፋሪ መጫኛ ቦታው ላይ ስትሪትካር በየአስራ ሁለት ደቂቃው ይደርሳል ማለት ነው። የስትሪትካር የመድረሻ ሰዓትን የአየርንብረት እና የትራፊክ ሁኔታዎች ተጽእኖ ሊፈጥሩበት ይችላሉ።
በዲሲ ስትሪትካር ላይ የሚያዙ የግል ዕቃዎች
ጋሪ የሚገፉ ሰዎች በዲሲ ስትሪትካር ላይ እንዲሳፈሩ ይፈቀድላቸዋል?
አዎ። የዲሲ ስትሪትካር ከመጫኛ መድረክ ጋር እኩል የሆኑ ሰፊ የተሳፋሪ በሮችን በመጠቀም ጋሪ የሚገፉ ሰዎች እንዲሳፈሩ ይፈቅዳል። በተጨማሪም፣ ተሽከርካሪው ብስክሌቶችን እና ዌልቼሮችን ማሳፈር ይችላል።
ብስክሌቶች በዲሲ ስትሪትካር ላይ እንዲሳፈሩ ይፈቀድላቸዋል?
አዎ። ቦታ ያለ ከሆነ፣ ዲሲ ስትሪትካር ብስክሌቶች እንዲሳፈሩ ይፈቅዳል። ከመጫኛው ቦታ ወለል ጋር እኩል የሆነ የመግቢያ ቦታ ለማግኘት የመሃለኛውን በር ይጠቀሙ። ምንም ዓይነት የውጭ እና የውስጥ የብስክሌት መጫኛዎች የሉም፣ ስለዚህ እባክዎ በሚሳፈሩበት ሰዓት ብስክሌቱን አያስተኙት። በተጨማሪም፣ ተሽከርካሪው ጋሪዎችን እና ዌልቼሮችን ማሳፈር ይችላል። እባክዎ ስትሪትካሮች ለብስክሌቶች ቦታ ላይኖራቸው ይችላል እና በቂ ቦታ ሲኖር ጊዜ ብቻ ይሳፈሩ።
የዲሲ ስትሪትካር ላይ የቤት እንስሳት/አገልግሎት ሰጪ እንስሳቶች ማሳፈር ይፈቀዳል?
አዎ፣ አገልግሎት ሰጪ እንስሳቶች ያለምንም መደርደሪያ ወይም ማቀፊያ ቤት አስፈላጊነት እንዲጫኑ ይፈቀድላቸዋል። በተጨማሪም የቤት እንስሳቶች እንዲሳፈሩ ይፈቀድላቸዋል፣ ሆኖም ግን፣ ሁሉም የቤት እንስሳቶች በመደርደሪያ ወይም ማቀፊያ ቤት ውስጥ መቀመጥ አለባቸው በተለይ ለእንሳስ ማጓጓዣነት የተሰሪ ዕቃዎችን መጠቀም እና በጉዞ ላይ እንስሳቶቹ መታሰር አለባቸው።
በዲሲ ስትሪትካር ላይ ምግብ መመገብ ይፈቀዳል?
በዲሲ ውስጥ የሚገኙ የመጓጓዣ መኪናዎች ላይ መብላት እና መጠጣት አይፈቀድም፣ ነገር ግን የዲሲ ስትሪትካር የታሸጉ አስቤዛዎችን የማጓጓዣ እና በመተላለፊያው ላይ የማስተላለፊያ ምርጡ መንገድ ነው።
የመኪና ማቆሚያ ስፍራ እና መንገድን ማግኘት
የስትሪትካር መንገድ አጠገብ መኪና ማቆም እችላለሁኝ?
በኤቭ ስትሪት ኤን ኢ (H Street NE) መንገድ ላይ መኪና ማቆም በሜትር ያስከፍላል እና ለ 2 ሰዓታት ብቻ የተገደበ ነው። የቤኒንግ (Benning) መንገድ እና በስፍራው ላይ የሚገኙ ሰፈሮች የመኪና ማቆም የተወስኑ እና በዞን የተከፋፈሉ ናቸው። የስትሪትካር መስመሮች ወይም ከነጩ መስመር ውጪ ደርበው የቆሙ ስትሪትካሩን የሚገቱ መኪናዎች ቅጣት ይጣልባቸዋል እና በመኪና ማንሻዎች እንዲነሱ ይደረጋሉ። የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በዩኒየን ጣቢያ (Union Station) እና አሬኤፍኬ ላይ የሚገኘው ዘ ፊልድስ (The Fields at RFK) ላይ ይገኛሉ።
ዲሲ ስትሪትካርን እንዴት ማግኘት እችላለሁኝ?
የዲሲ ስትሪትካር በአሁኑ ሰዓት 8 የተሳፋሪ መጫኛና ማውራጃ ቦታዎች አሉት። የተሳፋሪ መጫኛና ማውራጃ ቦታዎች ላይ የቅርብ መዳረሻ ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፦
ዩኒየን ስቴሽን (Union Station) – ሁሉም የመጓጓዣ ዘዴዎች አምትራክ (Amtrak)፣ ሜትሮ (ሬድ ላይን) [Metro (Red line)]፣ ማርክ (MARC)፣ ቪአርኢ (VRE)፣ የንግድ አውቶብሶች፣ ዲሲ ሰርኩሌተር (DC Circulator)፣ ታክሲዎች፣ ሜትሮባስ (Metrobus) (96፣ D6፣ D8፣ X2)። ካፒታል ባይክሼር (Capital Bikeshare)፣ እና የመኪና ማቆሚያ ገራጅ ጨምሮ
3rd St NE & H St NE – ሜትሮባስ (Metrobus) (D8)፣ ካፒታል ባይክሼር (Capital Bikeshare)
5th St NE & H St NE – ካፒታል ባይክሼር (Capital Bikeshare)
8th St NE & H St NE – ሜትሮባስ (Metrobus) (90, 92)፣ ካፒታል ባይክሼር (Capital Bikeshare)
13th St NE & H St NE – ካፒታል ባይክሼር (Capital Bikeshare)
15th St NE & H St NE – ሜትሮባስ (Metrobus) (B2፣ X2)፣ ካፒታል ባይክሼር (Capital Bikeshare)
19th St NE & Benning Rd NE
ኦክላሃማ መንገድ (Oklahoma Avenue NE) እና ቤኒንግ መንገድ( Benning Rd NE) – ካፒታል ባይክሼር (Capital Bikeshare), አሬኤፍኬ መኪና ማቆሚያ ላይ የሚገኘው ፊልድስ (Fields at RFK Parking)፣ ከስታዲየም-አርሞሪ ሜትሮ (Stadium-Armory Metro) የ 20 ደቂቃ የእግር መንገድ (ሰማያዊ/ብርትኳንማ መስመር)
የጠፉ እና የተገኙ ዕቃዎች
በስትሪትካር ውስጥ ዕቃ የጣልኩኝ ከሆነስ?
በዲሲ ስትሪትካር ላይ ዕቃ የጣሉ ከሆነ፣ በታቻለ ፍጥነት ቅጻችንን ሞልተው ያስረክቡን። እባካዎ የተጓዙበት የጉዞ መስመር፣ ሰዓት እና የጠፋውን ዕቃ ማብራሪያ ይፃፉልን። በተቻለን መጠን ዕቃውን ለማግኘት እና መልሰን ለእርስዎ ለመስጠት እንሞክራለን። እዚህ ላይ በመሄድ የበለጠ ይወቁ።
በድንገተኛ ጊዜ
የከፋ የአየር ንብረት ሁኔታ በሚፈጥርበት ሰዓት የዲሲ ስትሪትካር ላይ ምን ይፈጠራል?
ስትሪትካሮች በበረዶ እና ዝናባማ ሁኔታዎች ላይ በተሳካ ሁኔታ መስራት ይችላሉ፣ ነገር ግን ልክ እንደሌሎቹ ተሽከርካሪ መኪናዎች የከፋ የአየርንብረት እና የበረዶ ዶፍ ዝናብ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ውስንነት ሊኖራቸው ይችላል። የከፋ የአየር ንብረት ሁኔታ ሲፍጠር ጊዜ የአገልግሎት መቋረጦች ያሉ ከሆነ በመገናኛ ብዙሐን፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ እና ስትሪትካር መከታተያ መተግባሪያዎች ላይ መልዕክት ይተላለፋል።
የዲሲ ስትሪትካር መንገድ ላይ የተበላሸ ወይም የስትሪትካር መስመሮችን የሚዘጉ የመኪና አደጋዎች/ ግጭቶች ከተፈጠሩ ምን ይፈጥራል?
የዲሲ ስትሪትካር አደጋ ያጋጠመው ወይም መንገድ ላይ የተብላሽ ከሆነ፣ ስትሪትካር ልዩ በሆነ መኪና ተነስቶ ወደ ጥገና ስፍራ እንዲወሰድ ይደረጋል። የመኪናዎች አደጋ በሚፈጠርበት ወቅት፣ በተቻለ ፍጥነት የድንገተኛ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ቡድኖች ከስትሪትካር መንገድ ላይ መኪናዎቹን ያነሳሉ። ለአዳዲስ መረጃዎች እና ለአገልግሎት ማሳወቂያ መረጃዎች@DCStreetcar በትዊትር (Twitter) ላይ ይከታተሉ።
በስትሪትካር መንገድ ላይ ደርበው ያቆሙ መኪናዎች ቅጣት ይጣልባቸዋል እና በመኪና ማንሻ እንዲነሱ ይደረጋል።
ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች – ስለ ደህንነት እና ተደራሽነት
ስትሪትካሮች የ ADA ሕግን የሚያከብሩ ናቸው?
አዎ። ዘመናዊ የዲሲ ስትሪትካሮች ውስጥ ከተሳፋሪ መጫኛና ማውረጃው ወለል ጋር እኩል የሆኑ ሰፋፊ የተሳፋሪ በሮችን በመጠቀም ዌልቼሮቹን እና የሞተር ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት የተዘጋጁ ናቸው። ስትሪትካሮች ዌልቼሮችን እና የሞተር ተሽከርካራዎችን ለማስተናገድ በቂ የሆነ የማቆሚያ ቦታ ያላቸው እኩል የሆኑ ወለሎች አሏቸው። በተጨማሪም፣ ተሽከርካሪዎቹ ብስክሌቶችን እና ጋሪዎችን ማሳፈር ይችላሉ።
ስትሪትካር ውስጥ የመጫኛና ማውረጃ ቦታዎች ይነገራሉ?
በቅርብ ያሉ የመጫኛና ማውረጃ ቦታዎች ለተሳፋሪዎች ይነገራሉ።
ስለ ስትሪትካር ደህንነት የበለጠ እንዴት ለማወቅ እችላለሁኝ?
ስትሪትካር ውስጥ እና አቅራቢያ ላይ እንዴት ደህንነትዎን መጠበቅ እንደሚችሉ ለማወቅ የ ደህንነት ክፍልን ይጎብኙ።
የዲሲ ስትሪትካር መጓጓዣ መስመሮች የኤሌትሪክ ከረንት አላቸው?
የላቸውም። መስመሮቹ የኤሌትሪክ ከረንት የላቸውም። መስመሮቹ ቢራመዱባቸው አስተማማኝ ናቸው፣ ነገር ግን ብስክሌት እሽከርካሪዎች መስመሮቹ ላይ ጎማቸው እንዳይቀረቀር በትይዩ ሳይሆን በሰያፍ ሁኔታ መንዳት አለባቸው።
በዲሲ ስትሪትካር ላይ ጸጥታ አስከባሪዎች አሉ?
የአካባቢው ፖሊሶች መደበኛው የቅኝት ስራቸውን ለመተግበር የመጫኛና ማውረጃ ቦታዎች ላይ ይመጣሉ፣ እና በስትሪትካር ውስጥ ጸጥታ አስከባሪዎች አሉ።
ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች – ስትሪትካሮች
የስትሪትካር ሊንጎ በተመለከተ የቅርብ መረጃ ለማግኘት የ የዲሲ ስትሪትካር የቃላት መፍቻን ይመልከቱ።
ስትሪትካር ምንድን ነው?
ስትሪትካር የሕዝብ መጓጓዣ አውቶብሶች ሲሆኑ የሚሰሩት በሕዝብ መንገዶች ላይ በተቀመጡ የተወሰኑ የመተላለፊያ መስመሮች በኩል ነው። ተሽከርካሪዎቹ በተቀላቀለ የትራፊክ መንገድ እና/ወይም ራሱን የቻለ የተነጠለ መንገድ ላይይጓዛሉ። የዲሲ ስትሪትካር “ዘመናዊ ስትሪትካር” – ነው ይሄም ማለት የአየር መቆጣጠሪያ የተገጠመለት እና ከመጫኛና ማውረጃ ቦታው ወለል ጋር እኩል የሆነ ማለት ነው። ዝቅ ያለው ወለል ፈጣን እና ቀላል በሆነ መልኩ ሰው የመጫኛ ዕድል ይፈጥራል።
ስትሪትካር ትልቀቱ ምን ያህል ነው?
እያንዳንዱ ስትሪትካር ተሽከርካሪ ከ 144-160 የሚያህሉ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የተሳፋሪ መቀመጫዎች እና ማቆሚያዎችን አሉት። ስትሪትካሮች ልክ እንደማንኛውም አይነት አውቶብስ ተመሳሳይ ርዝመት ቢኖራችውም ብዙ ሰዎችን ይጭናሉ። ከታች ያለውን የማነጻጸሪያ ምስል ይመልከቱ፦
ስትሪትካር በምን ያህል ፍጥነት ይጓዛል?
ስትሪትካሮች በአካባቢው ልክ እንዳሉት አውቶብሶች በተመሳሳይ ፍጥነት ይጓዛል፣ ከተፈቀደላቸው ፍጥነት በላይ መጓዝ አይችሉም እና ካለው የትራፊክ ፍሰት ጋር ይጓዛሉ። አብዛኛው መተላለፊያ መስመር ላይ፣ ስትሪትካሮች ያሉትን የትራፊክ ምልክቶች ይከተላሉ።
ስትሪትካር ከቀላል ባቡር ወይም ከባቡር በምን ያህል ደረጃ ይለያል?
ምንም እንኳን ስትሪትካሮች እና ቀላል ባቡሮች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀሙ ቢሆንም፣ ልዩነት አላቸው። ስትሪትካሮች በተለምዶ አነስተኛ፣ ቀላል፣ በጣም ርካሽ፣ እና ለራሳቸው ብቻ የተዘጋጀ መንገድ ላይ ከመጓዝ ይልቅ በአብዛኛው የተቀላቀለ የትራፊክ መንገድ ላይ ይጓዛሉ።
የስትሪትካር ስርዓቶች በጣም በፍጥነት ሊገነቡ ይችላሉ፣ እና ይበልጥ በጣም ወጪ ቆጣቢ ናቸው፣ እና ከቀላል ባቡሮች ጋር ሲነጻጸሩ በግንባታ ወቅት አነስተኛ በሆነ ደረጃ የንግድ ተቋማትን እና የማህበረሰብን እንቅስቃሴን ያገታሉ። ስትሪትካሮች ብዙ ጊዜ ሊቆሙ ይችላሉ እና ለከተማው ሰፈሮች የሚጠቀሙ ይበልጥ ተገቢ የሆኑ አገልግሎቶች ይሰጣሉ።
ቀላል ባቡር በአብዛኛው የሚያገለግሉት በከተማና በከተማ አጎራባች ቦታዎች መካከል ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በፍጥነት ለማጓጓዝ የተዘጋጁ በአንፃሩ ፈጣን የሚባሉ ለክፍለ ሃገራት መጓጓዣነት የሚውሉ ትላልቅ ተሽከርካሪዎች ናቸው። ከባድ ባቡሮች (በዲሲ ሚትሮ አከባቢ ውስጥ እንደሚገኙት ዓይነት ሜትሮሬሎች) ለክፍለ ሃገራት እና ለረጅም ርቀት ትራንስፖርት ሊያገለግሉ ይችላሉ።
ስትሪትካሮች የሚረብሽ ድምጽ አላቸው?
ስትሪትካሮች ከተለመዱት አውቶብሶች በተለየ ድምጽ የላቸውም። የሚንቀሳቀሱት ድምጽ አልባ በሆኑ በኤሌክትሪክ ሞተሮች ነው፣ ስትሪትካሮች በሚጓዙብት መስመር ላይ በግምት 20 ጫማ ክፍታ ያለው የኤሌትሪክ ገመድ ጋር የተገናኘ የብረት ዘንግ በመጠቀም የኤሌትሪክ ኋይል ያገኛሉ። ከስትሪትካር የሚወጣው ድምጽ እንቅስቃሴን ለመከታተል ተብሎ ከተገጠመው ቸርኬ እንጂ፣ ልክ እንደ አውቶብስ ከሞተሩ ላይ የሚወጣ ድምጽ አይደለም።
ስትሪትካሮች በሚያልፉበት ሰዓት፣ ልክ እንደ ትላልቅ የጭነት መኪናዎች ወይም አውቶብሶች ንዝረትን ይፈጥራሉ?
አዎ። ከስትሪትካር የሚወጡ ንዝረቶች በዲሲ ሰርኩሌተር አውቶብሶች እንደሚወጡት ዓይነት ነው።
ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች – የስትሪትካር የምልክት ሁኔታ
የ ኤች መንገድ ኤን ኢ (H Street Ne)/ቤኒንግ መንገድ (Benning Road) ስትሪትካር የሚሄዱት መሃል ወይም የመንገድ ጠርዝ አቅራቢያ ነው?
ሁለቱም ላይ! የሆፕስኮች ድልድይ (Hopscotch Bridge) ላይ ስትሪትካር መሃል ላይ መጓዝ ይጀመራል፣ በመቀጠል በቤኒንግ መንገድ ላይ ሲገባ ጊዜ ወደ መሃል ቦታ እስከሚመጣበት፣ ከስታርበርስ ፕላዛ (Starburst Plaza) ድረስ የድልድዩ ታች ላይ በመንገዱ ጥግ ጠርዝ ላይ ይጓዛል።
ከሌሎች መኪናዎች እና እግረኛ መንገደኞች ጋር የተቀላቀለ ትራፊክ ያለበት የተጨናነቀ መንገድ ላይ ስትሪትካሮች እነዚህን መተላለፊያ መንገዶች እንዴት ያቋርጣሉ?
አብዛኛው መተላለፊያ መስመር ላይ፣ ስትሪትካሮች ያሉትን የትራፊክ ምልክቶች ይከተላሉ። ስትሪትካሮች የመኪና ትራፊክ መተላለፊያ መስመሮችን በሚያቋርጡበት ቦታ ላይ፣ ተጨማሪ ለስትሪትካሮች ብቻ የሚውሉ የትራፊክ ምልክቶች ተገጥመዋል። እነዚህ ምልክቶች ዌሰተርን ተርናራውንድ (Western Turnaround) [3ኛ መንገድ ኤን ኢ (3rd Street NE)]፣ የስታርበረስት መሳለጫ መንገድ (Starburst intersection) [15ኛው መንገድ ኤንኢ (15th Street NE)]፣ የካርን ባርን ማሰልጠኛ ማዕከል (Car Barn Training Center) [24ኛው መንገድ ኤንኢ] (24th Street NE) መግቢያ ላይ እና ኢስተርን ተረንአራውንድ (Eastern Turnaround) [ኦክላሃማ መንገድ ኤንኢ (Oklahoma Avenue NE)] ላይ ይገኛሉ። ተቆጣጣሪዎቹ ለስትሪትካር አሽከርካሪዎች በመተላለፊያ መንገድ ወይም የጋራ መተላለፊያ መንገዶች ላይ መቼ መጓዝ እንደሚችሉ ይነግሯቸዋል።
የስትሪትካር ብቻ መንገድ ምልክቶች ምን ይመስላሉ?
ምንም እንኳን የስትሪትካር መንገድ ምልክቶች ከመደበኛ መኪና የትራፊክ መብራት ምልክቶች ጋር አብረው የተገጠሙ ቢሆንም፣ ለመደበኛው አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ወይም ቀይ መብራት ጋር ሊያሳስቱ አይችሉም። የስትሪትካሮች ለመለየት ደማቅ ቀለማትን ከመጠቀም ይልቅ፣ ፈካ ያለ ቀይ ወይም ነጭ መስመሮች ያገለግላሉ። የመብራት ምልክቶቹ አናት እንደ የስትሪትካር እንደሚሄድበት ሁኔታ በአግድም፣ በሰያፍ ውይም በቁም መስመሮችን ያበራሉ። በነባሪ ሁኔታ የማንኛውም ባቡር መቆጣጠሪያ መብራት ምልክት የቁም ምልክት ነው፣ ይሄ በአግድም በተሰመረ ቀይ መስመር ይለያል። ስትሪትካሮች በማሳለጫ መንገዶች ላይ ሲቀጥሉ ጊዜ፣ የስትሪትካር መብራት ካሉት ሶስት አቅጣጫዎች ውስጥ፡ ግራ፣ ቀኝ ወይም አግድም መስመሮች ላይ የሚያመላክት ነጭ መብራት ያሳያል።
የዲሲ ስትሪትካር-ብቻ መንገድ መብራት ስትሪትካር ብቻ መምጣቱን በምን ይለያል?
የምልክት መስመሮቹ ለሕዝብ ከመታየታቸው በፊት ብዙ ያልታዩ እርምጃዎች መታየት አለባቸው። የስትሪትካር መተላልፊያ መስመሮች ላይ የተገጠሙ የእንቅስቃሴ መለያዎች ይለዩታል እና የስትሪትካር ሲቃረብ ብቻ ይበራሉ። አሽከርካሪው በስትሪትካር ውስጥ የተገጠመ ማብራያና ማጥፊያ አዝራርን በመጫን በዚህ ጊዜ ላይ በራስሰር ለተገጠመው የመቆጣጠሪያ ስርዓት የስትሪትካሩን አቅጣጫ ይጠቁማል። የተለያዩ የራስሰር የፍተሻ ተግባራት ይከናወናሉ እና ስትሪትካሩ ምልክት መስጠት አስተማማኝ በሚሆንበት ጊዜ ላይ ብቻ ምልክት ይሰጣል።
አሽከርካሪዎች የሚተላለፉበት እና እግረኛ መንገደኞች መንገድ የሚያቁርጡብት ጊዜ መቼ ነው?
ሁሉንም ምልክቶች በጥንቃቄ መመልከት ጠቃሚ ነው። መደበኛ የተሽከርካሪ መኪናዎች ጉዞ እና የእግረኛ መንገዶች መንገድ ማቋረጥ ተግባር የሚከናወነው ስትሪትካሩ መሳለጫ መንገዱን ሲያልፍ እና የመኪና ትራፊክ መብራት አረንጓዴ ሲያበራ ጊዜ ነው። በአብዛኛው ጊዜ ላይ፣ ቀይ የመኪና መብራት የሚጠቁመው ስትሪትካር መንገድ አረንጓዴ እንደሆነ ነው።
ስትሪትካሮች በሚጓጓዙብት ሰዓት ተሳፋሪዎች ደህንነታቸው እንዴት መጠበቅ ይችላሉ?
ልክ እንደ ሁልጊዜ፣ እግረኛ መንገደኞች እና አሽከርካሪዎች መተላለፊያ መንገዶችን በሚያቋርጡበት ሰዓት ጥንቃቄ መውሰድ አለባቸው። “ማየት፣ ማዳመጥ፣ ጥንቃቄ ማድረግን” ያስታውሱ።